Add Listing

ኮኬት

Profit Analysis
Visit Now
  • Viewed - 4
  • Bookmark - 0

Telegram Description

ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ። https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv "መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው…."

Latest Channel Posts

Channel Image
ገበያ አይዋሽም!

የእንቁላል ዋጋ ተወዷል። ጾም ገብቶም ዋጋው አልወረደም። ይህ ለምን ሆነ? ይህ የሆነው ለገበያው እየቀረበ ያለው የእንቁላል መጠን ከፍላጎቱ ያነሰ ስለሆነ ነው።

የእንቁላል ዋጋ ወርዶ 5 ብር የደረሰበት ጊዜ ነበር። ያኔ ብዙ የእንቁላል ዶሮ የሚያረባ ሰው ነበር። ሆኖም የመኖ ዋጋ ውድ ነበር። አርቢውም ከዛሬ ነገ ይሻላል በሚል እየከሰረ ዶሮ ማርባቱን ቀጠለ።

መኖ ለምን ተወደደ? የመኖ ዋና ግብዓቶች በቆሎና አኩሪ አተር በፀጥታ ችግር፣ ከውጭ የሚመጡ ግብዓቶች ዋጋ ደግሞ በዶላር ምንዛሪ መወደድ ምክንያት የመኖ ዋጋ ናረ። በዚህ የተነሳ ዶሮ አርቢዎቹ ከሰሩ። በኪሳራ መቀጠልም አልቻሉም። መኖ መግዣ እስኪያጡ ተቸገሩ።

የከሰሩ አርቢዎች የገና በዓልን ጠብቀው የእንቁላል ዶሮዎችን ለበዓል እርድ ሸጡ። ከዚያ በኋላ የእንቁላል እጥረት ተፈጠረ፤ ዋጋውም ቀስ እያለ ወደላይ ወጣ። ከ8 ብር ተነስቶ 9፣ 10፣ 12፣ 15፣ 17 እያለ የእንቁላል ዋጋ 20 ብር ገባ። አሁን መኖውን የሚመጥን ዋጋ ላይ ነው።

የሁዳዴ ጾም ሲገባ የእንቁላል ዋጋ ይቀንሳል ቢባልም ዋጋው አልቀነሰም። ምክንያቱም ፍላጎቱ አልቀነሰም። የረመዳን መግባትም ዋጋውን እንዳይቀንስ ያደርገዋል።

Trust the market. ገበያን እመነው። ገበያ አይዋሽም። ገበያ የሚመራው በአቅርቦትና ፍላጎት የሚዛን ጨዋታ ነው። ዋጋ የሚንረውም፣ ግርግር የሚበዛውም እጥረት ሲኖር ነው።

ገበያን እመነው!

የነዳጅ እጥረት አለ። ለዚህ ምልክቱ በየቦታው የሚታየው ሰልፍ ነው። እጥረት ከሌለ በቀር ያ ሁላ ሰልፍ አይኖርም። በቂ ነዳጅ አለ ቢባልም በየማደያው ያለው ሰልፍ አሳሳቢና እጥረት መኖሩን ጠቋሚ ነው።

በተለይ የናፍጣ እጥረት አሳሳቢ ነው። የጭነት መኪና ሲቆም የሸቀጦች አቅርቦት ይዳከማል፣ ዋጋቸውም ይንራል። ነገሩ ተያያዥ ነው። ችግሩን ለመፍታት ግን ውስብስብ አይደለም።

እንዲህ እጥረት ሲኖር የነዳጅ ዋጋ በኩንትሮባንድ ይሀን በቀጥታ ዋጋው ይጨምራል። መንግስትም የዋጋ ጭማሪ ያደርጋል።

እያለ እያለ የወር ወጪህ ይንራል።

የኢኮኖሚው ብልሃት ገና አልተገኘም።

እንደ ህዝብ ብዛታችን በአስደንጋጭ ፍጥነት ወደ ላይ እየተተኮሰ ነው። አሁን ከ130 ሚሊየን በላይ ሆነናል። ከዓለም ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ቀድሞ ከነበርንበት 12ኛ ደረጄ ጃፓንና ሜክሲኮን ቀድመን 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠናል። ኢኮኖሚያችን ግን 100ኛ ደረጃ ላይም የለም።

የህዝብ ቁጥር ሲያድግ ፍላጎት ይጨምራል። ምግብ ልብስ መጠለያ፣ መድሃኒት፣ ነዳጅ፣... ፍላጎታቸው ይጨምራል። በዚያው ልክ አቅርቦት ካልጨመረ በስተቀር የፍላጎት ናዳው ችግር ውስጥ ይከተናል።

መፍትሔው አንድና አንድ ነው። አቅርቦትን መጨመር!

አቅርቦት ለመጨመር ምርትን ማብዛት ነው። ለዚህ መፍትሔው ታክስ ቀንሶ አምራች ኢንቨስተርን መሳብ፣ ሠራተኛን ማሰልጠን፣ መሬት በስፋት ማቅረብ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ማስፋት ናቸው። እነዚህ ሁሉ ግን የፖሊሲ ማሻሻያ ይፈልጋሉ።

የፖሊሲ ለውጥ በ6 ወራት ውስጥ የተጠበቀው ውጤት ካልታየ ችግር አለ።

የኢኮኖሚያችን መፍትሔ ብዙ ምርምር አይፈልግም። ያልታረሱትን መሬቶች ማረስ፣ ታክስ ቀንሶ ኢንቨስተሮችን መሳብ፣ የንግድ ስርዓቱ ላይ ያለ ቁጥጥርን መቀነስ፣ የፀጥታ ችግርን መፍትሔ መስጠት እና የመንግስት ሠራተኛን ቀንሶ አምራች ኃይል ማድረግ ናቸው።

ለምን ዙሪያ ጥምጥም እንደምንሄድ አይገባኝም።

የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ምን እያደረገ ነው?

ከየትም የሚገኝ ጠቃሚ ተሞክሮ ስናይ ትምህርት ወስዶ መፍትሔ ማምጣት ላይ ማተኮር አስፈላጊ ነው።

ገበያ አይዋሽም! ኑሮ ከተወደደ ችግሩ ያለው ፖሊሲው ላይ ነው።

https://t.me/+6o1ZHgKbYAA2ODc8
2025-03-01T03:11:55+00:00
Channel Image
👉👉የማስታወቂያ ጊዜ 👈👈

#1.አኪያ የእንጨት ሥራ  የተለያዩ  የዋንዛ፡ የወይራ፡ የቀረሮ እና የጽድ እንጨት ውጤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን ኑ ወደ ቤታችሁ!!
https://t.me/+D6VnZzXYklFiODc0

#2. አኪባ ደላላ (Akiba brokers)
ማንኛውም ቤት፣ ቦታ፣ መኪና
መግዛት ወይም መሸጥ ካሰቡ በቴሌግራም @Akiba2121 ያናግሩን
👉አላማችን በታማኝነት በመሥራት የገዥዎች እና የሻጮችን ድካም ማስቀረት ነው።
https://t.me/+mEB8K9ALTOE2N2Q8

#3.Free Market (ነፃ ገቢያ)
#በነፃ ገበያ #በነፃ ይሸጡ #በነፃ ይግዙ
➥ኑ ወደ በነፃ ገበያ
👉 https://t.me/+8-xyDsd40bgxMzc0
 

#4.ኮኬት ዶሮ እርባታ እና እንቁላል ማከፋፈያ
ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ  Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv

#5.የኢትዮጽያ ወተት ላም እርባታ
ይህ Group ስለ ወተት ላም እንድሁም አጠቃላይ ስለ ከብት ዕርባታ የምንወያይበት እና ከባለሙያዎች የምክር አገልግሎት ምናገኝበት ነው።
https://t.me/+ckwmrjSK6282Yjdk

#6.ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ በነፃ ስለ business ግንዛቤ ለማግኘት ትክክለኛ ቦታ 👉https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0
የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

#7. የኢትዮጵያ የእንቁላል ገቢያ
እንቁላል ለመግዛት ለመሸጥ ይን group ይጠቀሙ
https://t.me/+jkaTTT3oupo1MGM0

         👇
የተለያዩ የbusiness ሀሳብ ላይ የ Telegram group ወይ channel ያላችሁ በዚህ "የማስታወቂያ ጊዜ" መመዝገብ ከምትፈልገው በዚህ link 👉 @sewhun13 👈 አናግሩን
2024-12-28T13:58:39+00:00
Channel Image
የዶሮዎችን መነካከስ መፍትሄው ምን ይሁን'?
https://t.me/koketi2012poultry
👉ለ ዶሮ መነካከስ እንደ መፍትሄ የምንጠቀማቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ:: ዛሬ የምንመለከተው በዋናነት መፍትሄ ናቸው ያልናቸውን ነው:: በተለይ ጀማሪ ዶሮ አርቢዎች በዚህ ነገር በጣም ሲቸገሩ እንመለከታለን:: አሁን መፍትሄውን በ ሁለት ከፍለን እናያለን::
👉የመጀመሪያው ቅድመ መከላከል ነው:: ይሄ ማለት መነካከስ እንዳይፈጠር ቀድመን መውሰድ የሚገባን እርምጃዎች ሲሆኑ በሁለተኛው ላይ የምናየው ደሞ መነካከስ ከተከሰተ በዋላ እንዴት ማከም እንዳለብን እንመለከታለን:: ለ ቅድመ መከላከሉ ከምናስቀምጠው ውስጥ:-
ሀ/ አረጓዴ ተክሎችን መስጠት
ለ/በተከለለ ስፍራ ላይ መልቀቅ
ሐ/ የሚያፀባርቅ ነገር ከ አጠገባቸው ማረግ
መ/ ማንቁር መቁረጥ
ሀ/ አረንጓዴ ተክሎችን መስጠት
👉 ዶሮዎች አረንጓዴን ተክሎችን በመመገባቸው በዋነኚነት በምግባቸው ውስጥ የ ፋይበር ክምችት ከፍ እንዲል ያደርጋል:: የ ፋይበር ክምችት ከፍ ሲል ደሞ ጨጓራ ቶሎ ስለሚሞላ እና ስለሚጠግቡ መነካከሱን በ እጅጉን ይቀንሳል::
👉 ሌላው አረንጓዴ ነገር ስንሰጣቸው ቀኑን ሙሉ ትኩረታቸው እሱ ላይ ስለሚሆን ወደ መነካከስ እንዳይፈጠር ይረዳል::
👉 ዶሮዎች መነካከስ ከጀመሩ ለማስቆም ስለሚከብድ እንደዚህ ቀላል የ ቅድመ መከላከል መንገዶችን በመጠቀም ዶሮዎችን ምርታማነታቸውን ዝቅ እንዳይል ማረግ እንችላለን::
ለ/ በተከለለ ስፍራ ላይ መልቀቅ
👉 በተከለለ ሰፍራ ስንል ዶሮዎቹ ከመኖሪያ ቤታቸው ጠዋት ላይ ወተው ሰፋ ባለና ሳራማ አካባቢ መልቀቅ ነው:: ያም ዶሮዎችን ቀኑን ሙሉ ቅጠላቅጠል እና ጉንዳኖችን እና ትላትሎችን እየበሉ ትኩረታቸውን እሱ ላይ ብቻ እንዲያረጉ ማረግ ይቻላል::
👉 ይሄ የቀድመ ጥንቃቄ ግን አሁን ለለንበት ለዘመናዊ የዶሮ አረባብ ብዙ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል:: በተለይ ዶሮዎችን በምንለቅበት ጊዜ ለተለያዪ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸውን ይጨምራል:: ግን እንደ ቅደመ ጥንቃቄ መውሰድ እንችላለን::
https://t.me/koketi2012poultry
ሐ/ የሚያንፀባርቅ ነገር ከ አጠገባቸው ማረግ
👉 እንደዚህ አይነት ቴክኒኮችን የምንጠቀመው በቀላሉ ዶሮዎች ከመነካከስ ለመከላከል ነው:: ዶሮዎች በባህሪያቸው አዲስ ነገር ላይ አይናቸውን ከሱ ላይ አያነሱም:: ለ ቅድመ ጥንቃቄ እንደ መፍትሄ ተደርጎ የሚቀመጠው በ እርባታ ቦታ የሚያንፀባርቅ ነገር ከ እንገታቸው ከፍ ተደርጎ መስቀል ነው:: በዚህን ጊዜ በተሰቀለው ነገር ብቻ ትኩረታቸውን ስለሚያረጉ መነካሱ እጅጉን ይቀንሳል:: እዚህ ጋር ግን ማሳሰብ ሚያስፈልገው የሚያንፀባርቀው ነገር ብዙ ብርሀን ሚያመነጭ መሆን የለበትም:: ምክንያቱም አይናቸው ቀጥታ ተጋላጭ ስለሚሆን::
👉 ሌላው የምንጠቀመው  አንፀባራቂው ነገር እንደ ቦታው ይወሰናል::  ማለት እንደሚረባው ዶሮ ብዛት እና እንደይዘው ቦታ ስፋት  ይወሰናል ማለት ነው::  እንደዚህ ቀላል የሆኑ ቅድመ ጥንቃቄዎችን በመውሰድ በእርባታ ውስጥ ያሉ ዶሮዎች ምርታማነታቸውን እንዳይቀንሱ ማረግ ይቻላል::
መ/ ማንቁር መቁረጥ
👉ማንቁር መቁረጥ በእርባታ ውስጥ የመጨረሻው መፍትሄ ቢሆን ይመረጣል:: ማንቁር መቁረጥ እንደ መፍትሄ የሚጠቅመው አንዳድ ዶሮዎች በ ዝርያ ደረጃ በባህሪ ተናዳጅ የሆኑ አሉ:: ለነሱ ብንጠቀም ተመራጭ ነው:: ሌላው ማንቁር መቆረጥ ያለበት ከ 8ሳምንታቸው  በዋላ መሆን አለበት:: ያም የሚመከረው ማንቁራቸው ጠንከር ማለት ስላለበት እና ወዲያው ስሚያድግ ነው::
👉 ማንቁር ለመቁረጥ የራሱ የሆነ መሳሪያ አለው:: መሳሪያው በዶሮች እድሜ እና ማንቁር መጠን የተዘጋጀ  ስለሆነ እንደምንፈልገው አርገን  መጠቀም እንችላለን:: በዚህ ስራህ ላይ የሚሰሩ የራሱ የሆኑ ባለሞያዎች ስላሉት በባለሞያ የታገዘ ማንቁር ቆረጣ ቢደረግ ይመረጣል::
👉 አንዳድ እርባታ ቦታ ላይ የማንቁር መቁረጫ ማሽን ባለመገኘቱ በመቀስ ሲቆርጡ ይታያል:: ይሄ ግን ተገቢ አይደለም::ዶሮዎች ላይ ሊደርስ የሚችለው የማንቁር መቁሰል ጭራሽ ዶሮዋ መመገብ እንዳትችል ስለሚያረጋት አይመከርም:: በባለሞያ የታገዘ ቢሆን ይመረጣል:: ስለዚህ በቀላሉ ማንቁር በመቁረጥ በዶሮች መሀል የሚደርሰውን ቁስለት እና ሞት በማስቀረት ምርታማነትን ከፍ ማረግ ይቻላል::

https://t.me/koketi2012poultry
2024-10-24T03:44:10+00:00
Channel Image
👉👉የማስታወቂያ ጊዜ 👈👈

#1.Free Market (ነፃ ገቢያ)
#በነፃ ገበያ #በነፃ ይሸጡ #በነፃ ይግዙ
➥ኑ ወደ በነፃ ገበያ
👉 https://t.me/+8-xyDsd40bgxMzc0

#2. አኪባ ደላላ (Akiba brokers)
ማንኛውም ቤት፣ ቦታ፣ መኪና
መግዛት ወይም መሸጥ ካሰቡ በቴሌግራም @Akiba2121 ያናግሩን
👉አላማችን በታማኝነት በመሥራት የገዥዎች እና የሻጮችን ድካም ማስቀረት ነው።
https://t.me/+mEB8K9ALTOE2N2Q8

#3.አኪያ የእንጨት ሥራ  የተለያዩ  የዋንዛ፡ የወይራ፡ የቀረሮ እና የጽድ እንጨት ውጤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን ኑ ወደ ቤታችሁ!!
https://t.me/+D6VnZzXYklFiODc0
 

#4.ኮኬት ዶሮ እርባታ እና እንቁላል ማከፋፈያ
ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ  Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv

#5.የኢትዮጽያ ወተት ላም እርባታ
ይህ Group ስለ ወተት ላም እንድሁም አጠቃላይ ስለ ከብት ዕርባታ የምንወያይበት እና ከባለሙያዎች የምክር አገልግሎት ምናገኝበት ነው።
https://t.me/+ckwmrjSK6282Yjdk

#6.ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ በነፃ ስለ business ግንዛቤ ለማግኘት ትክክለኛ ቦታ 👉https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0
የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

#7. የኢትዮጵያ የእንቁላል ገቢያ
እንቁላል ለመግዛት ለመሸጥ ይን group ይጠቀሙ
https://t.me/+jkaTTT3oupo1MGM0

         👇
የተለያዩ የbusiness ሀሳብ ላይ የ Telegram group ወይ channel ያላችሁ በዚህ "የማስታወቂያ ጊዜ" መመዝገብ ከምትፈልገው በዚህ link 👉 @sewhun13 👈 አናግሩን
2024-10-04T05:47:10+00:00
Channel Image
👉🏾በዶሮ እርባታ ውስጥ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብዙ ጥቅሞች አሉት-

📌 ቅልጥፍናን መጨመር፡-   ቴክኖሎጂ በዶሮ እርባታ ላይ ያሉ እንደ መመገብ እና ውሃ ማጠጣት ያሉ ብዙ ስራዎችን በራስ ሰር እንዲሰራ ይረዳል ይህም ቅልጥፍናን ለመጨመር እና የሰው ኃይል ወጪን ለመቀነስ ያስችላል።

📌 የተሻሻለ ክትትል፡-   ቴክኖሎጂ አርቢዎች የዶሮ ጤናን እና ባህሪን በብቃት እንዲቆጣጠሩ ያግዛል። ለምሳሌ የሙቀት መጠንን እና የአየር እርጥበት ለውጦችን ለመለየት ሴንሰሮች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ  ይህም አርቢዎች ችግሮች ከመድረሳቸው በፊት ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለይተው እንዲያውቁ ይረዳል.

📌 የተሻለ መዝገብ መያዝ፡-
   ቴክኖሎጂ አርቢዎች የምገባ መርሃ ግብሮችን፣ የመድሃኒት አስተዳደርን እና የምርት መረጃዎችን ጨምሮ የስራቸውን ትክክለኛ እና አጠቃላይ መዛግብትን እንዲይዙ ይረዳቸዋል። ይህ መረጃ አዝማሚያዎችን ለመለየት እና የበለጠ በመረጃ የተደገፈ የአስተዳደር ውሳኔዎችን ለማድረግ ሊያገለግል ይችላል።

📌 የተሻሻለ ባዮሴኪዩሪቲ፡
    ቴክኖሎጂ ወደ ተቋሙ የሚገባው ማን ላይ የተሻለ ቁጥጥር በማድረግ፣ ጎብኝዎችን በመከታተል እና የበሽታውን ወረርሽኞች በመለየት በዶሮ እርባታ ላይ ያለውን የባዮሴኪዩሪቲ ለማሻሻል ይረዳል።

📌 ከፍተኛ የምርት መጠን፡-   እንደ የተሻሻለ የመብራት እና የሙቀት መቆጣጠሪያ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አርቢዎች የዶሮችን ሁኔታን በማሻሻል ከፍተኛ የምርት መጠን ማግኘት ይችላሉ።

‼️ ቴክኖሎጂ የዶሮ እርባታ አርቢዎች በተቀላጠፈ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ይረዳል ይህም የዶሮችን ደህንነት ማሻሻል  ምርት መጨመር እና ከፍተኛ ትርፍ ያስገኛል.
2024-09-27T05:11:20+00:00
Channel Image
👉🏾በዶሮ እርባታ ውስጥ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብዙ ጥቅሞች አሉት-

📌 ቅልጥፍናን መጨመር፡-   ቴክኖሎጂ በዶሮ እርባታ ላይ ያሉ እንደ መመገብ እና ውሃ ማጠጣት ያሉ ብዙ ስራዎችን በራስ ሰር እንዲሰራ ይረዳል ይህም ቅልጥፍናን ለመጨመር እና የሰው ኃይል ወጪን ለመቀነስ ያስችላል።

📌 የተሻሻለ ክትትል፡-   ቴክኖሎጂ አርቢዎች የዶሮ ጤናን እና ባህሪን በብቃት እንዲቆጣጠሩ ያግዛል። ለምሳሌ የሙቀት መጠንን እና የአየር እርጥበት ለውጦችን ለመለየት ሴንሰሮች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ  ይህም አርቢዎች ችግሮች ከመድረሳቸው በፊት ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለይተው እንዲያውቁ ይረዳል.

📌 የተሻለ መዝገብ መያዝ፡-
   ቴክኖሎጂ አርቢዎች የምገባ መርሃ ግብሮችን፣ የመድሃኒት አስተዳደርን እና የምርት መረጃዎችን ጨምሮ የስራቸውን ትክክለኛ እና አጠቃላይ መዛግብትን እንዲይዙ ይረዳቸዋል። ይህ መረጃ አዝማሚያዎችን ለመለየት እና የበለጠ በመረጃ የተደገፈ የአስተዳደር ውሳኔዎችን ለማድረግ ሊያገለግል ይችላል።

📌 የተሻሻለ ባዮሴኪዩሪቲ፡
    ቴክኖሎጂ ወደ ተቋሙ የሚገባው ማን ላይ የተሻለ ቁጥጥር በማድረግ፣ ጎብኝዎችን በመከታተል እና የበሽታውን ወረርሽኞች በመለየት በዶሮ እርባታ ላይ ያለውን የባዮሴኪዩሪቲ ለማሻሻል ይረዳል።

📌 ከፍተኛ የምርት መጠን፡-   እንደ የተሻሻለ የመብራት እና የሙቀት መቆጣጠሪያ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አርቢዎች የዶሮችን ሁኔታን በማሻሻል ከፍተኛ የምርት መጠን ማግኘት ይችላሉ።

‼️ ቴክኖሎጂ የዶሮ እርባታ አርቢዎች በተቀላጠፈ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ይረዳል ይህም የዶሮችን ደህንነት ማሻሻል  ምርት መጨመር እና ከፍተኛ ትርፍ ያስገኛል.
2024-07-03T04:32:11+00:00

GPT Description

Related Video

No video available.

Item Reviews - 0

No reviews yet.

Add Review

Location for : Listing Title